ስለ እኛ

የእኛ ታሪክ

የአቅመ ደካማ አዛውንቶች የኑሮ ትግል የልብ ሸክም በሆነባቸውና የትውልድ ስራ መፍታት በሚያሳስባቸው ቅን ልብ ባላቸው 15 በሃገር ውስጥና በውጪ ሃገር በሚኖሩ በጎ ፍቃደኛ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ሴቶች፤ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት የተቀመጠውን መስፈርት በማሟላት የሶሪ ሱቅ ብሩህ ተስፋ መረጃ ዕድር ስም ተመዝግቦ ያለምንም ልዩነት ችግረኞችን፤ ደሃ አደጎችንና ረጂ አልባዎችን ለመርዳትና የወደቁትን አቅም በፈቀደ መጠን ሌሎች ወገኖችንም አስተባብሮ ለማገዝ በከፍተኛ መሰጠትና ውሳኔ መስከረም 4 ቀን 2018 ዓ.ም ተቋቋመ።

መስራች አባላት

የሶሪ ሱቅ ብሩህ ተስፋ መረዳጃ ዕድር መስራች አባላት ስም ዝርዝር እና የስራ ኃላፊነት የሚከተለው ነው።

አቶ አብርሃም መኰንን

ሰብሳቢ

አቶ እንዳለ ቢረሳው

ም/ሰብሳቢ

ወ/ሪት ዘላለም አበበ

ፀሀፊ

አቶ ቃልኪዳን አስማማው

ገንዘብ ያዥ

ወ/ሮ ንጋት ኃይሉ

ሂሳብ ሹም

ሻምበል ዘላለም ታምራት

ኦዲትና ቁጥጥር ኮሚቴ

አቶ ያሬድ አረጋ

ኦዲትና ቁጥጥር ኮሚቴ

አቶ ደረጄ አጥናፉ

ኦዲትና ቁጥጥር ኮሚቴ

ወ/ሮ ሙሉዓለም ረጋሳ

የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ

ወ/ሮ እጅጋየሁ በቀለ

የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ

ወ/ሪት ሀይማኖት አፅበሀ

ትምህርት እና ስልጠና

አቶ ሰውነት አበበ

ትምህርት እና ስልጠና

ወ/ሮ ኢየሱሳዊት ጌታቸው

ትምህርት እና ስልጠና

ወ/ሮ ጀምበር ወ/ጊዮርጊስ

ትምህርት እና ስልጠና

ዶ/ር ፍቃዱ መኰንን

ትምህርት እና ስልጠና

መስራች አባላት

የሶሪ ሱቅ ብሩህ ተስፋ መረዳጃ ዕድር መስራች አባላት ስም ዝርዝር እና የስራ ኃላፊነት የሚከተለው ነው።

አቶ አብርሃም መኰንን

ሰብሳቢ

አቶ እንዳለ ቢረሳው

ም/ሰብሳቢ

ወ/ሪት ዘላለም አበበ

ፀሀፊ

አቶ ቃልኪዳን አስማማው

ገንዘብ ያዥ

ወ/ሮ ንጋት ኃይለ

ሂሳብ ሹም

ሻምበል ዘላለም ታምራት

ኦዲትና ቁጥጥር ኮሚቴ

አቶ ያሬድ አረጋ

ኦዲትና ቁጥጥር ኮሚቴ

አቶ ደረጄ አጥናፉ

ኦዲትና ቁጥጥር ኮሚቴ

ወ/ሮ ሙሉዓለም ረጋሳ

የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ

ወ/ሮ እጅጋየሁ በቀለ

የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ

ወ/ሪት ሀይማኖት አፅበሀ

ትምህርት እና ስልጠና

አቶ ሰውነት አበበ

ትምህርት እና ስልጠና

ወ/ሮ ኢየሱሳዊት ጌታቸው

ትምህርት እና ስልጠና

ወ/ሮ ጀምበር ወ/ጊዮርጊስ

ትምህርት እና ስልጠና

ዶ/ር ፍቃዱ መኰንን

ትምህርት እና ስልጠና

ዓላማዎች

የሶሪ ሱቅ ብሩህ ተስፋ መረዳጃ ዕድር ዓላማዎች፡

በተለያዩ ምክንያቶች የተጎዱ የማህበረሰባችን ክፍሎች ያለምንም ልዩነት የሚስፈልጋቸውን የገንዘብ፣ የጉልበት፣ የስልጠናና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎች መስጠት፣

በስራ ማጣትና በተለያዩ የኑሮ ጉዳቶች የተቸገሩ ሰዎችን በሙያ ስልጠና፣ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ድጋፎች በማገዝ ኑሯቸውን ማሻሻልና ራሳቸውን ማስቻል፣

በማህበረሰቡ ውስጥ የእርስ በርስ የመደጋገፍ ባህልን በማጠናከር የተጎዱና የተረሱ ወገኖችን ራሳቸውን የሚችሉበትን መንገድ በማመቻቸት ለሌሎች አርዓያ እንዲሆኑ ማስቻል።

የትኩረት ቡድኖች

  • አቅመ ደካማ አዛውንቶች፤
  • የጤና እክል የገጠማቸው ወገኖች፤
  • የትምህርት መሳሪያ አቅም ውስንነት ያለባቸው ህፃናት፤
  • በተለያየ የአቅም ውስንነት ምክንያት መስራት ያልቻሉ ወገኖች፤

እቅዶቻችን

የሶሪ ሱቅ ብሩህ ተስፋ መረዳጃ ዕድር የሚከተሉት የአጭር ጊዜ፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅዶች ይኖሩታል።

የአጭር ጊዜ ዕቅድ(0 - 2 አመት)

  • በዕድሜ የገፉ አዛውንቶችንና የጤና እክል የገጠማቸውን ሰዎች በገንዘብና በቁሳቁስ ማገዝ፤
  • ለተቸገሩ ወላጆች ሆነ ልጆቻቸው አስፈላጊ የምግብ፣ የአልባሳትና የትምህርት ቁሳቁስ በግዢ ማቅረብ፤
  • የአቅመ ደካሞችንና ድጋፍ የሚሹ ሰዎችን ቤት ማጽዳት፤
  • የአዛውንቶችንና የአቅመ ደካሞች ቤት እንደአስፈላጊነቱ ማደስ፤

የመካከለኛ ጊዜ ዕቅድ(2 - 5 አመት)

  • ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ጋር ትስስር መፍጠር፤
  • የገቢ ማስገኛ ስልቶችን በመንደፍ ዘላቂ ገቢ ማመንጨት፤
  • ከሃገር ውስጥና ከውጪ ሃገራት ገቢ ማግኛ ፕሮጀክት በመቅረፅና ሃብት በማሰባሰብ ቋሚ የገቢ ድርጅቶችን ማቋቋም፤

የረጅም ጊዜ ዕቅድ(5+ አመት)

  • የተገኙ ጠቃሚ ልምዶችን በመጠቀም አገልግሎቱን በሃገር አቀፍ ደረጃ ማስፋፋት፤
  • ለአዛውንቶችና ለተጎዱ ወገኖች የማገገሚያ ማዕከላት ማቋቋም፤
Scroll to Top

የእርስዎ ደግነት የለዉጥ ተልዕኳችንን ይደግፋል

ይለግሱ

ንግድ ባንክ: 1000720593727
ሶሪ ሱቅ ብሩህ ተስፋ መረዳጃ እድር

+251 929 376 362‬
+251 713 344962‬

አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ

info@sorishopbrighthope.org

አንድ ላይ ሆነን ዘላቂ ተፅዕኖ መፍጠር እንችላለን!

አሁኑኑ ይቀላቀሉን

አንድ ላይ፣ ብዙ ህይወት መለወጥ እንችላለን።

አጋር ይሁኑን