አገልግሎቶቻችን

የእኛ አገልግሎቶች

ዘላቂ እና አዎንታዊ ለውጥ የሚፈጥሩ ግለሰቦች በማስተማር የተሻለ ነገን እንዲገነቡ በሚያበረታቱ ማህበረሰብ ተኮር ፕሮግራሞች ላይ እናተኩራለን። 

ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የምግብ፣ አልባሳትና ጤና አገልግሎት፣

አስፈላጊ የሆኑ የምግብ እቃዎችን፣ አልባሳትን እና መሰረታዊ የጤና አጠባበቅ አገልግሎቶችን በችግር ላይ ላሉ ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች ማቅረብ።

ለአዛውንቶች የድጋፍና የእንክብካቤ አገልግሎት፤

ለአረጋውያን የማያቋርጥ የድጋፍ እና የእንክብካቤ አገልግሎት በመስጠት፣ ክብርን፣ ምቾትን እንዲሁም በህብረተሰቡ ውስጥ አካታችነትን ማረጋገጥ።

የህይወት ክህሎትና የሙያ ስልጠና አገልግሎት፤

የህይወት ክህሎት ትምህርት እና የሙያዊ ስልጠና ፕሮግራሞችን በመስጠት አዳዲስ የስራ እድሎች ላይ በማተኮር ስራ ፈጣሪነትን ማበረታታት።

ለአካል ጉዳተኞች የትምህርትና አጋዥ ቁሳቁሶች፤

ለአካል ጉዳተኛ ወገኖች ትምህርት ጨምሮ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችን መከታተል ለማስቻል የመማሪያ ግብዓቶችን እና አጋዥ መሳሪያዎችን ማቅረብ።

ስትራቴጂዎች

የሶሪ ሱቅ ብሩህ ተስፋ መረዳጃ ዕድር የአተገባበር ስትራቴጂዎች፤

1

ለአዛውንቶችና የጤና እክል ለገጠማቸው ወገኖች የጤናና ተዛማጅ እንክብካቤ ማድረግ፣

2

የኑሮ ጉዳት ላለባቸውና ስራ አጥ ወገኖች በቴክኖሎጂ የታገዘ ሙያዊ ስልጠናና የገንዘብ ድጋፍ በማመቻቸት ራሳቸውን በዘላቂነት እንዲችሉ ማገዝ፣

3

ፍትሃዊና ጥራት ያለው አገልግሎት በዘላቂነት ተጠቃሚዎች ማድረግ፤

4

ተአማኒና የተሻለ አገራዊ ተጽዕኖ ለማምጣት ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት

አሁን ይመዝገቡ

Scroll to Top

የእርስዎ ደግነት የለዉጥ ተልዕኳችንን ይደግፋል

ይለግሱ

ንግድ ባንክ: 1000720593727
ሶሪ ሱቅ ብሩህ ተስፋ መረዳጃ እድር

+251 929 376 362‬
+251 713 344962‬

አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ

info@sorishopbrighthope.org

አንድ ላይ ሆነን ዘላቂ ተፅዕኖ መፍጠር እንችላለን!

አሁኑኑ ይቀላቀሉን

አንድ ላይ፣ ብዙ ህይወት መለወጥ እንችላለን።

አጋር ይሁኑን